News Alert - Amharic | Dec 23,2025
Jan 17 , 2026
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ለኢትዮጵያ የ48 ወራት የብድር ፕሮግራም አፈጻጸም አራተኛውን ዙር ግምገማ ካጠናቀቀ በኋላ የ261 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ እንዲለቀቅ ወሰነ። ባለፈው ሐሙስ በዋሽንግተን ዲሲ የተሰበሰበው የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ያሳለፈው ይህ ውሳኔ እ.ኤ.አ. በ2024 አጋማሽ የጸደቀውን የ3.4 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ድጋፍ ተከትሎ እስካሁን የተለቀቀውን የገንዘብ መጠን 2.18 ቢሊዮን ዶላር አድርሶታል። ይህ በሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ድርጅቱ ከሚሰጠው የገንዘብ ድርሻ አንጻር ከፍተኛው የድጋፍ መጠን ነው።
አይ ኤም ኤፍ በቅርብ ግምገማው የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም “ከሚጠበቀው በላይ” ሲል አወድሶታል። ድርጅቱ ለዚህ በማሳያነት የጠቀሰው መሻሻል የታየበትን የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት፣ የኤክስፖርት ገቢ መጨመርን፣ የተሻሻለ የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ማደግን እና የዋጋ ግሽበት መቀዝቀዝን ነው። ዓርብ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አይ ኤም ኤፍ "ሁሉም የአፈጻጸም መስፈርቶች የተሟሉ ሲሆን አብዛኞቹ አመላካች ግቦችም ተሳክተዋል" ብሏል።
ይሁን እንጂ የቦርዱ ይሁንታ በጥንቃቄ የታጀበ ነበር። የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናይጄል ክላርክ በምንዛሬና በገንዘብ ፖሊሲው ላይ የታዩ ለውጦችን ቢያደንቁም በ2018 ዓ.ም. የፌዴራል በጀት ላይ የታዩ መዛባቶች ቀደም ሲል ከተስማሙት የፋይናንስ ማዕቀፎች ውጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል። መንግሥት ይህንን የበጀት መዛባት ለማስተካከልና የፋይናንስ ዲስፕሊን ለመጠበቅ ቃል የገባ ሲሆን በብሩክ ታየ (ዶ/ር) የሚመራው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ኦዲት የተደረገ የፋይናንስ መግለጫ አለመታተሙም ሌላኛው እንደ ክፍተት የተጠቀሰ ጉዳይ ነው።
በአዲሱ ስምምነት መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ገበያ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት የሚገድብ አዲስ ገደብ ተቀምጧል። ይህም ባንኩ የውጭ ምንዛሬ እንቅስቃሴውን በይፋ ጨረታ ብቻ እንዲያከናውን የሚያስገድድ ሲሆን ዓላማውም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተዳደር ላይ የሚሰነዘሩ የግልጽነት ጥያቄዎችን ለመመለስና በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ እምነትን ለመገንባት ነው።
በተጨማሪም አይ ኤም ኤፍ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ እንዲቀጥል እና የነዳጅ ድጎማ ደረጃ በደረጃ እንዲነሳ በድጋሚ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ የዕዳ ሸክም አሁንም በፕሮግራሙ ላይ ጥላውን ያሳረፈ ሲሆን ከሁለትዮሽ አበዳሪዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ቢፈረምም ከግል አበዳሪዎች ጋር ያለው ድርድር እስካሁን ባለመቋጨቱ ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል። እ.ኤ.አ. በ2023 የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ክፍያ ባለመፈጸሟ በይፋ "ዲፎልት" ውስጥ የገባችው ኢትዮጵያ ሹሞቿ ውስብስብ የዕዳ ሽግሽግ ድርድሮችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ። መንግሥት ከኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት ውጭ አዳዲስ የንግድ ብድሮችን ከመውሰድ እንዲቆጠብም ድርጅቱ አሳስቧል።
Photo Gallery | 192142 Views | May 06,2019
Photo Gallery | 181911 Views | Apr 26,2019
Photo Gallery | 178645 Views | Oct 06,2021
My Opinion | 144166 Views | Aug 14,2021
Jul 25 , 2026
Ideally, citizens who have paid income tax all year should not have to reach for thei...
Jul 18 , 2026
Pressed in Parliament on jobs and household incomes, Prime Minister Abiy Ahmed (PhD)...
Jul 11 , 2026
At a market stall, reform arrives without a communique. It comes as a higher transpor...
Jul 4 , 2026
In the goldfields of the Benishangul-Gumuz Regional State, Ethiopia's balance-of-paym...