Feb 4 , 2026.
ጸደይ ባንክ የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የቀድሞውን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ዮሐንስ አያሌውን (ዶ/ር) በፕሬዝዳንትነት ለመሰየም ተዘጋጅቷል።
በአማራ ክልል ከነበረው የብድርና ቁጠባ ተቋምነት ወደ ባንክ ካደገ በኋላ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ሊሆን የሚችለውን ዕጩ ለይቷል። ይህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ባንኩ በባለፈው ሒሳብ ዓመት የ2.13 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ባጋጠመው ወሳኝ ወቅት ላይ የቀረበ ነው።
ዮሐንስ በብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት ካገኙ ባለፈው ጥር ወር ላይ ስልጣን የለቀቁትን የጸዳይ ባንክ መስራች ፕሬዝዳንት መኮንን የለውምወሰንን የሚተኩ ሲሆን፤ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ የሺእመቤት ተፈራ ባንኩን በጊዜያዊነት በመምራት ላይ ይገኛሉ።
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የሥራ ልምድ ያላቸው ዮሐንስ፣ የቀድሞ የሙያ ዘመናቸው ለዘጠኝ ዓመታት በብሔራዊ ባንክ ዋና የምጣኔ ሀብት ባለሙያነት የተቃኘ ነበር። በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እንዲሁም በአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ልማት ኢንሹራንስ የሀገር ውስጥ ዳይሬክተር በመሆንም አገልግለዋል። በተለይም እ.ጎ.አ ከ2018 እስከ 2022 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቆዩባቸው ዓመታት ተቋሙን ከተከማቸ የማይመለስ ብድር በማላቀቅ ወደ ንግድ ተኮር የብድር አሰጣጥ ለማሸጋገር ያደረጉት ጥረት ውጤት የታየበት እንደነበር ይታወሳል። ዮሐንስ በቅርቡ የአማራ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው በሰሩባቸው 16 ወራት ባንኩ በገንዘብ እጥረትና በውስጥ ቀውስ ውስጥ በነበረበት ወቅት ተረክበውት፣ ከኪሳራ በማውጣት 655 ሚሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ እንዲያስመዘግብና የ85 በመቶ ዕድገት እንዲያሳይ ማስቻላቸው ይታወሳል።
PUBLISHED ON
Feb 04,2026 [ VOL
26 , NO
1345]
Photo Gallery | 192130 Views | May 06,2019
Photo Gallery | 181900 Views | Apr 26,2019
Photo Gallery | 178633 Views | Oct 06,2021
My Opinion | 144154 Views | Aug 14,2021
Jul 25 , 2026
Ideally, citizens who have paid income tax all year should not have to reach for thei...
Jul 18 , 2026
Pressed in Parliament on jobs and household incomes, Prime Minister Abiy Ahmed (PhD)...
Jul 11 , 2026
At a market stall, reform arrives without a communique. It comes as a higher transpor...
Jul 4 , 2026
In the goldfields of the Benishangul-Gumuz Regional State, Ethiopia's balance-of-paym...