FORTUNE+ VIDEO SPONSORED CONTENTS ADVERTORIALS FORTUNE AUDIO Fortune Careers TRADE AFRICA Election 2026 New TIME REMAINING UNTIL ETHIOPIA’S NATIONAL ELECTION 0Days 0Hours 0Minutes 0Seconds


ለልማት ባንክ አምስት አዳዲስ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተሾሙ

Jan 12 , 2026.


​መንግሥታዊው የፖሊሲ ባንክ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (ኢልባ) በአመራር እርከኑ ላይ አምስት አዳዲስ ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ዛሬ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አግኝቷል።

​የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ብሩክ ታየ (ዶ/ር) በባንኩ ውስጥ ረጅም ዘመን ያገለገሉትን ጌታቸው ዋቄን በመተካት የኔነህ ግዛውን የኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል። በተመሳሳይ ጌታሰው ፈንታው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ዘርፍን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመድበዋል።

​አቶ ጌታቸው በላይ የኮርፖሬት ደንበኞች አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት፤ አበባው ሲራጅ የፋይናንስና ዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት፤ እና ደሳለኝ ኃይሌ የኢንፎርሜሽን ሲስተምና ዲጂታል ባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

​የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ብሩክ፣ የቀድሞውን የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተክተው የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑ ወዲህ በባንኩ የአመራር መዋቅር ላይ ፈጣን ለውጦች እየታዩ ነው። ሰሞኑን እመቤት መለሰን (ዶ/ር) በመተካት የባንኩ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን መሥራች አመራርነት በብሩክ ሥር ሲሠሩ የቆዩ መሆኑ ይታወሳል።

​ፎርቹን የተመለከተው የቦርድ ሰብሳቢው የሹመት ደብዳቤና መግለጫ እንደሚያሳየው፣ አዲሶቹ ተሿሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሙሉ ቁርጠኝነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።



PUBLISHED ON Jan 12,2026 [ VOL 26 , NO 1342]


[ssba-buttons]

Editorial