Photo Gallery | 185860 Views | May 06,2019
Dec 30 , 2025.
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራር እርከን ላይ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩት ጌታቸው ዋቄ ከታኅሣሥ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ከባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል። የጌታቸው መሰናበት በባንኩ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሰፊ የአመራር ለውጥ አካል ሲሆን፣ በቅርብ ሣምንታት ካስተናገዳቸው ከፍተኛ የአመራር ሽግሽጎች መካከል አንዱ ሆኗል።
ጌታቸው ከባንኩ የተሰናበቱት ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በተለያዩ ስትራቴጂካዊ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ካገለገሉ በኋላ ነው። የእሳቸው ስንብት የመጣው፣ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በባንኩ የሥራ አስፈጻሚዎችና በዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ላይ እየተደረገ ካለው ተከታታይ ለውጥ ጋር ተገጣጥሞ ነው።
ቀደም ሲል ተክለወልድ አጥናፉን በመተካት፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታየ (ዶ/ር) የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። ተክለወልድ ለረዥም ዔመታት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ሰርተዋል::
የብሩክ ሹመት በባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ሹመትና መዋቅራዊ የሥልጣን ወሰን ላይ ካሉ ውጥረቶች ጋር ተያይዞ፣ ተቋሙ አዲስ የአመራር አቅጣጫ እንዲይዝ የሚያደርግ ሊሆን ይችላል።
በዚሁ የአመራር ለውጥ ሂደት፣ ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር) እመቤት መለሰን (ዶ/ር) በመተካት የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። ኢሳያስ ቀደም ሲል በብሩክ መሪነት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ውስጥ ያገለገሉ ሲሆን፣ የሳቸው ወደ ልማት ባንክ መምጣት ተቋሙ በሥራ አስፈፃሚ አባላት ላይ ለውጥ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ብሩክ በሰጡት መግለጫ፣ ጌታቸው ለባንኩ ላበረከቱት የረጅም ዘመን አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበው ከምክትል ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸው መሰናበታቸውን አረጋግጠዋል።
PUBLISHED ON
Dec 30,2025 [ VOL
26 , NO
1340]
Photo Gallery | 185860 Views | May 06,2019
Photo Gallery | 175901 Views | Apr 26,2019
Photo Gallery | 171460 Views | Oct 06,2021
My Opinion | 139414 Views | Aug 14,2021
May 9 , 2026
The Ethiopian state appears to have discovered a fiscal instrument that is politicall...
May 2 , 2026
By the time Ethiopia's National Dialogue Commission (ENDC) reached the end of its fir...
Apr 25 , 2026
In a political community, official speeches show what governments want their citizens...
For much of the past three decades, Ethiopia occupied a familiar place in the Western...