Photo Gallery | 189860 Views | May 06,2019
Jan 9 , 2026.
በአለም አቀፍ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ግዙፍ ስም ያለው ካርፎር፣ ከሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት የኩዊንስ ሱፐርማርኬትን ተክቶ ስራ ሊጀምር ነው።
በጀማል አህመድ የሚመራው የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ በስራ ላይ የሚገኙትን 13 የኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቅርንጫፎች በሙሉ ወደ ካርፎር የንግድ ምልክት ለመቀየር ተስማምቷል። የሽግግሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ በጎርጎሮሳውያን ዘመን እስከ 2026 አጋማሽ ድረስ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥም ተጨማሪ 17 አዳዲስ የካርፎር መደብሮችን ለመክፈት እቅድ ተይዟል።
ፈረንሳይ ውስጥ በ1950ዎቹ የተመሰረተው ካርፎር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የ"ሃይፐር ማርኬት" (Hypermarket) የንግድ ዘይቤን በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ እንደሆነ ይታወቃል። ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከ40 በላይ ሃገራት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በ30 ሃገራት ውስጥ ከሚገኙ 3,000 የፍራንቻይዝ መደብሮች ጋር በመሆን በአጠቃላይ ወደ 15,000 የሚጠጉ መደብሮች አሉት። በፈረንጆቹ 2024 ዐመተ ምህረት የ94.6 ቢሊዮን ዩሮ የሽያጭ ገቢ ያስመዘገበው ካርፎር፣ በገቢ መጠኑ ከአለማችን ግዙፍ የችርቻሮ ተቋማት ተርታ ይሰለፋል። ኩባንያው በያዝነው ዓመት በ10 አዳዲስ ሃገራት ስራውን ለማስፋፋት እየሰራ ይገኛል።
በተለይ ትኩስ አትክልትና ፍራፍሬዎችን "ከእርሻ ወደ ገበታ" የአቅርቦት ሰንሰለቱ የሚታወቀው ኩዊንስ ሱፐርማርኬት፣ በዚህ የንግድ ሽርክና መሰረታዊ ለውጦችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል። በካርፎር ስር የሚደራጁት መደብሮች ከምግብ ነክ ምርቶች በተጨማሪ እንደ የቤት እና የቢሮ ቁሳቁሶች፣ የማብሰያ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን በማካተት አገልግሎታቸውን እንደሚያሰፉ ይጠበቃል።
PUBLISHED ON
Jan 09,2026 [ VOL
26 , NO
1341]
Photo Gallery | 189860 Views | May 06,2019
Photo Gallery | 179585 Views | Apr 26,2019
Photo Gallery | 176219 Views | Oct 06,2021
My Opinion | 141920 Views | Aug 14,2021
Jun 13 , 2026
The recent policy decision to fully open freight forwarding to foreign capital may be...
Jun 6 , 2026
For a political veteran as controversial as Getachew Reda, last week's national elect...
May 30 , 2026
Tomorrow, millions of Ethiopians are expected to vote in the seventh national electio...
May 23 , 2026
An International Monetary Fund (IMF) team has spent weeks in Addis Abeba conducting t...