FORTUNE+ VIDEO SPONSORED CONTENTS ADVERTORIALS FORTUNE AUDIO Fortune Careers TRADE AFRICA Election 2026 New TIME REMAINING UNTIL ETHIOPIA’S NATIONAL ELECTION 0Days 0Hours 0Minutes 0Seconds



አዲስአበባ (ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም) — ንስር ማይ ክሮፋይናንስ ከካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ጋር ባደረገው ስትራቴጂካዊ ትብብር ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶቹን የሚያዘምንበትንና ተደራሽነቱን የሚያሰፋበትን "ንስርከፍታ" የተሰኘ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ አስተዋወቀ። አገልግሎቱም በፕሌይስቶር (Play Store) እና በአፕልስቶር (App Store) በሚገኘው የንስር ማይክሮፋይናንስ ሞባይል መተግበሪያ (Nisir Microfinance App) በኩል ለደንበኞች መስጠት ጀምሯል።

በዘርፉ ከ10 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ንስር ማይክሮፋይናንስ ፣ ቀደም ሲል ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ በአካል በመምጣት ቀናት ይወስድባቸው የነበረውን የፋይናንስ አገልግሎት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በማድረግ ደንበኞች ባሉበት ሆነው ፣ በማንኛውም ሰዓት በደቂቃዎች ውስጥ ማግኘት የሚያስችላቸውን አሰራር ዘርግቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ የቴክኖሎጂና የዲጂታል መተግበሪያ አቅርቦት ድርሻውን ተወጥቷል።

በዚህ አዲስ አገልግሎት ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ በአካል መሄድ ሳይጠበቅባቸው በስልካቸው የንስር ማይክሮፋይናንስ መተግበሪያን በመጠቀም፦


  • የተለያዩ የዲጂታል ቁጠባ አገልግሎቶች በጋራ የሚንቀሳቀሱ የቁጠባ ሂሳቦችን (Joint Accounts) ጨምሮ፣
  • የዲጂታል የጊዜ ገደብ ቁጠባ ሂሳብ (Digital TimeDeposit) ፣

  • ለጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች የሚሰጥ የዲጂታል ብድር፣

  • ለደመወዝተኞች የሚቀርብ የደመወዝ መዳረሻ ብድር (Salary Advance) ፣
  • የኢንሹራንስ እረቦን ክፍያ ብድር (Insurance Premium Financing) ፣
  • ደንበኞች የቁጠባ ሂሳባቸውን እንደጠበቁ በሂሳብ እንቅስቃሴያቸው ላይ የተመሰረተ የአጭር ጊዜ የካሽ ብድር (Cash Loan based on Account Operation) ፣ እና ሌሎች የንስር ማይክሮፋይናንስ አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።

  • የንስር ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ እምቢአለ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት "ከካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ጋር የጀመርነው ጉዞ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለመረዳትና ከቴክኖሎጂ እድገት ጋር እኩል ለመራመድ ያደረግነውን ቁርጠኝነት የሚያሳይነው" ብለዋል።

    የካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ጥላሁን በበኩላቸው "የፋይናንስ ተቋማት ከዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በጥምረት መስራታቸው የሚሰጡትን አገልግሎት ማህበረሰብ ተኮር የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ ከአገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ጋር እኩል በመራመድ በተለመደው የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ መንገድ (Conventional way) የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግና እውነተኛ የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል" ሲሉ ገልጸዋል።

    ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ህግና ደንብ ተከተሎ ከ10 በላይ ከሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ጠንካራ አጋርነት በመመስረት አካታች የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ሲያቀርብ የቆየ ተቋም ነው። በአሁኑ ወቅት ከንስር ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር የተለያዩ የዲጂታል ቁጠባ፣ ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች እና ደመወዝተኞች የሚቀርቡ ብድሮችን፣ በሂሳብ እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ የካሽ ብድር እንዲሁም የኢንሹራንስ እርቦን ክፍያ ብድር (Insurance Premium Financing) አገልግሎቶችን በማስፋፋት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም የፋይናንስ ተቋማትን በዲጂታል ሲስተም በመደገፍ፣ ቀደምሲል በወሰን ቅርንጫፎች ተገድበው የነበሩ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን በUSSD እና በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት በጊዜና ቦታ ሳይወሰኑ ለደንበኞች ተደራሽ የማድረግ ስራእየሰራ ይገኛል።



    PUBLISHED ON Aug 13,2026 [ VOL 27 , NO 1372]


    [ratemypost]



    [ssba-buttons]

    Put your comments here

    N.B: A submit button will appear once you fill out all the required fields.


    Editors' Pick



    Editorial