FORTUNE+ VIDEO SPONSORED CONTENTS ADVERTORIALS FORTUNE AUDIO Fortune Careers TRADE AFRICA Election 2026 New TIME REMAINING UNTIL ETHIOPIA’S NATIONAL ELECTION 0Days 0Hours 0Minutes 0Seconds


ኢትዮጵያና ህንድ ከቪዛ ነፃ የዲፕሎማቲክ ጉዞ ተስማሙ

Jan 15 , 2026.


ኢትዮጵያና ህንድ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለያዙ ዜጎቻቸው ያለ ቪዛ እንዲመላለሱ የሚያስችል ስምምነት በይፋ ተፈራረሙ። ዛሬ ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረገ የዲፕሎማቲክ ማስታወሻ ልውውጥ ስምምነቱ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር ተሻግሯል።

በህንድ ኤምባሲ በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የእስያ እና የፓሲፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ደዋኖ ከዲር ሰነዶቹን ተለዋውጠዋል።

አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ እንደገለጹት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የብዙ ዜጎች ከቪዛ መዘግየት ነጻ ሆነው ጉዟቸውን መጀመር የሚችሉ ሲሆን የሚመለከታቸው ባለስልጣናት ምንም አይነት የፈቃድ ማረጋገጫ ሳይጠብቁ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ መጓዝ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል።

ይህ የቪዛ ነጻ ስምምነት በቅርብ ወራት ውስጥ እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት አጋርነት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት እ.ኤ.አ በታህሳስ 2025 አጋማሽ ላይ የህንድ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ባደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወቅት በዲጂታል መሰረተ ልማት ረገድ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል የዳታ ማዕከል ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።



PUBLISHED ON Jan 15,2026 [ VOL 26 , NO 1342]


[ssba-buttons]

Editorial