ኢግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ግሩፕ እና ፀደይ ባንክ በሀገራችን የግብርና ግብዓት ሥርጭትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ቀልጣፋና ግልጽ ለማድረግ የሚያስችል ታሪካዊ የስምምነት ሰነድ በትናንትናው ዕለት በፀደይ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል ፡፡
በዚህ ትብብር መሠረት የኢግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ግሩፕ የፈጠራ ውጤት የሆነው "Get Fee" የተሰኘው ዲጂታል ሲስተም ሥራ ላይ የሚውል ሲሆን፣ አሠራሩ ከኤጀንሲዎች እስከ አርሶአደሮች ድረስ ያለውን የግብርና ግብዓት ሥርጭት ሂደት በጥራትና በስፋት ለማከናወን ያስችላል፡፡
የኢግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በእርሱፈቃድ ጌታቸው እንደገለጹት፣ ድርጅታቸው በፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከ26 በላይ ምርቶችን በማበልፅግ ለገበያ ያቀረበና አሁንም ቴክኒዎሎጂን በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል Get Fee በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች እየተጠቀሙበት የሚገኝ የግብዓት ማሠራጫ ሲስተም ነው፡፡
ሲስተሙ ከፍተኛ ገንዘብ በሥርዓት እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል ትልቅ አቅም ያለው መሆኑንና በጥሬ ገንዘብ በሚደረጉ ግብይቶች ምክንያት የሚከሰቱ የሀብት ምዝበራዎችንና ተያያዥ ስጋቶችን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ዘመናዊና ግልጽ አሠራርን ለመተግበር የሚያስችል መሆኑን አቶ በእርሱፈቃድ አብራርተዋል፡፡
አክለውም፣ ለግብርናው ዘርፍ መዘመንና ለምርት እድገት ላለፉት 30 ዓመታት በገጠሩ ማኅበረሰብ ውስጥ ሰፊ መሠረት ጥሎ ሲሠራ ከቆየው አንጋፋው ፀደይ ባንክ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸው፣ ስምምነቱን በአጭር ቀናት ውስጥ ወደ ሙሉ ተግባር ለማስገባት ድርጅታቸው ሙሉ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፀደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው፣ ይህ ትብብር ባንኩ እያከናወናቸው ከሚገኙ ታላላቅ የማሻሻያ ሥራዎች መካከል ትልቁን ቦታ የሚይዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አሠራሩ የግብዓት ሥርጭትን በማዘመን ከአርሦ አደሮች ጀምሮ የበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎችንና የተቋማትን መሠረታዊ ችግር እንደሚፈታ የጠቆሙት ዶክተር ዮሐንስ፣ እያንዳንዱ ክፍያ ግልጽነት ባለው መንገድ እንዲያልፍ በማድረግ የሀገር ሀብት በጥቅም ላይ እንዲውል የማድረጉ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
Eaglelion system technology Group,
Ethiopian Company!
PUBLISHED ON
Aug 26,2026 [ VOL
27 , NO
1374]
Commentaries | Jan 31,2026
Editorial | Jul 07,2024
Viewpoints | Dec 20,2025
Fortune News | Jul 13,2024
View From Arada | May 09,2026
Radar | Mar 16,2024
Agenda | Jul 06,2025
Delicate Number | Nov 30,2024
Commentaries | Jun 13,2026
Dec 22 , 2024 . By TIZITA SHEWAFERAW
Charged with transforming colossal state-owned enterprises into modern and competitiv...
Aug 18 , 2024 . By AKSAH ITALO
Although predictable Yonas Zerihun's job in the ride-hailing service is not immune to...
Jul 28 , 2024 . By TIZITA SHEWAFERAW
Unhabitual, perhaps too many, Samuel Gebreyohannes, 38, used to occasionally enjoy a couple of beers at breakfast. However, he recently swit...
Jul 13 , 2024 . By AKSAH ITALO
Investors who rely on tractors, trucks, and field vehicles for commuting, transporting commodities, and f...
Aug 22 , 2026
A record is a strange thing to worry about. Federal trade officials have booked the b...
Aug 14 , 2026
Aschalew Fetene, known as “Ardi” and admired for his poetic depth, has built a ti...
Aug 8 , 2026
The World Bank asks readers to picture a mother in rural Ethiopia who has never held...
Jul 31 , 2026
Weldu Yiheysh has not read the Pacific temperature charts. He does not need to. In Shibta District of Enderta Wereda, in...