May 26 , 2026.
የኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ በስካይላይት ሆቴል የካፒታል ገበያን ተቀላቅሏል። ኩቢንያው በመጀመሪያ ደረጃ የካፒታል ገበያ (IPO) ባደረገው የአክሲዮን ሽያጭ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መሳብ ቢችልም፣ ካቀደው የፋይናንስ ግብ ግን በእጅጉ ያነሰ ካፒታል ይዞ ወደ ሁለተኛ ደረጃ የገበያ መድረክ (Secondary Market) ተሻግሯል።
የኢትዮ ቴሌኮም በገበያው ላይ በይፋ መመዝገብ፣ አዲሱ የካፒታል ገበያ ማዕቀፍ እውን ከሆነ ወዲህ የታየ እጅግ ጉልህ ምዕራፍ ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህ እርምጃ ትኩረቱን “የህዝብ ባለቤትነት ማረጋገጥ” ከሚለው አዋጅ ፈቀቅ በማድረግ፣ ወደ ተወሳሰበ የባለአክሲዮኖች ምዝገባ፣ የትርፍ ድርሻ መብት፣ የቁጥጥር ግልጽነት እና የገበያው ተአማኒነት ጥያቄዎች ላይ እንዲያርፍ አድርጎታል። የካፒታል ገበያው አሁንም ቢሆን “በአዳዲስ ሊበራል ልሂቃን የሚመራ” ሂደት ተደርጎ የሚወሰደውን የህዝብ ጥርጣሬ የመቀየር ከባድ ፈተና ከፊቱ ይጠብቀዋል።
ይህ ጅማሮ የመጣው መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ አክሲዮን ለህዝብ ግልጽ ሽያጭ ካቀረበ በኋላ ሲሆን፣ የአንዱ አክሲዮን መነሻ ዋጋ (Par value) ከሁለት ዓመት በፊት የተወሰነውን 310 ብር መሠረት ያደረገ ነበር። ነገር ግን የተመዘገቡት ውጤቶች የተስፋ እና የውስንነት ድብልቅ ሆነዋል። ወደ 47,377 የሚጠጉ ዜጎች በአክሲዮን ሽያጩ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ይህንን ውጤት በፋይናንስ ስርዓቱ ውስጥ የህዝብ ባለቤትነት ስር መስደዱን የሚያሳይ ማረጋገጫ አድርገው አቅርበውታል። ሆኖም፣ በተግባር የተሰበሰበው 3.2 ቢሊዮን ብር መንግስት ካለመው የ30 ቢሊዮን ብር ግብ ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ መሆኑ፣ በለውጥ ፍላጎት ፍጥነት እና የሀገር ውስጥ ቁጠባን በስፋት የማንቀሳቀስ አቅም መካከል ያለውን ሰፊ ክፍተት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
የካፒታል ገበያ ተቋማት ከህግ ማዕቀፍ ወጥተው በተግባር ወደሚሰራ የንግድ ስነ-ምህዳር መሸጋገር መቻላቸውን የሚመዝንበት ትልቅ ሚዛን ቢሆንም በዚህ ሂደት አክሲዮን ገዢዎችን በቀላሉ ወደሚሸጡና ወደሚለወጡ የባለቤትነት መዝገቦች የመቀየር ብቃት ገና በጅምሩ ተፈትኗል።
ከገዢዎቹ መካከል 45,000 የሚጠጉት የደንበኛ ማንነት ማረጋገጫ መስፈርቶችን አሟልተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በሂደቱ 96 በመቶ የሚሆኑትን ባለአክሲዮኖች በዲጂታል መዝገብ ማስፈሩን ይፋ ቢያደርግም፣ ስኬቱ ግን ከጎላ ክፍተት የጸዳ አልነበረም። በድምሩ 1,646 ባለአክሲዮኖች የማንነት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ሳያሟሉ የቀሩ ሲሆን፣ 248 ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በዜግነት ገደብ ምክንያት ያደረጉት የአክሲዮን ግዢ ሙከራ ውድቅ ተደርጓል።
“ብሔራዊ መታወቂያ ማቅረብ ለሚችሉ ሰዎች አክሲዮኑን እናጸድቃለን። ማቅረብ ለማይችሉ ግን የአገልግሎት ክፍያውን ጨምሮ ገንዘባቸውን እንመልሳለን” ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።
የአክሲዮን ሽያጩ በይፋ የተጀመረው በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ስነ-ስርዓት ነበር። ሽያጩ ለ121 ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም ተዘግቷል። በወቅቱ አንድ ባለአክሲዎን በትንሹ 9,900 ብር የሚያወጡ 33 አክሲዮኖችን፣ እና 999,900 ብር ዋጋ ያላቸው 3,333 አክሲዮኖችን መግዛት እንዲችል ተፈቅዶ ነበር። የሽያጩ ሂደት ሆን ተብሎ ለአነስተኛ እና ግለሰብ ባለሀብቶች ተሳትፎ ሚዛን የደፋ ቢሆንም፣ አጠቃላይ ውጤቱ ግን ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛ ዙር የአክሲዮን ሽያጭ ላይ እንዲያስብ አስገድዶታል። ይህ ቀጣይ እርምጃ ተቋማዊ ባለሀብቶችን (Institutional Investors) እና ምናልባትም የውጭ ሀገር ተሳታፊዎችን ለማካተት የነበሩ ገደቦችን ሊያላላ እንደሚችል ይገመታል።
የገበያ ተንታኞች እንደሚሉት፣ እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ “የባለሀብቱን መሠረት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰፋ ቢሆንም፣ አሁን ያሉትን የዜግነት ገደቦች ከወደፊቱ የውጭ ገዢዎች ተሳትፎ ጋር እንዴት ማስታረቅ ይቻላል?” የሚሉ የህግ ጥያቄዎችን ማስከተሉ አይቀሬ ነው።
የምዝገባው ይፋ መሆን የትርፍ ክፍፍል (Dividend) ውዝግብን ይበልጥ ወደ አደባባይ አውጥቶታል። አዲሶቹ የግል ባለአክሲዮኖች፣ ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 162 ቢሊዮን ብር ከፍተኛ ገቢ ማስመዝገቡ ቢገለጽም፣ እስከ ሐምሌ 2017 ዓ.ም. ላለው የበጀት ዓመት ምንም ዓይነት የትርፍ ክፍፍል አያገኙም። ካለፈው በጀት ዓመት የተገኘውና ይፋ የተደረገው 12 ቢሊዮን ብር የትርፍ ድርሻ ሙሉ በሙሉ የተከፈለው ለፌዴራል መንግሥት ነው።
ይህ ውሳኔ በፋይናንስ ባለሙያዎችና በባለአክሲዮኖች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እያሰናዳ ይገኛል። ተቺዎች እንደሚከራከሩት፣ የባለአክሲዮኖችን ህጋዊ እውቅና ማዘግየት ገና በማቆጥቆጥ ላይ ባለው የካፒታል ገበያ ላይ እምነትን የሚያሸረሽር ከመሆኑም በላይ፣ በንግድ ህጉ ላይ የባለአክሲዮኖች እውቅና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ መከናወን አለበት ከሚለውን ድንጋጌ የሚጋጭ ነው።
አዲሱ ገበያ ዜጎችን “የአክሲዮን ባለቤትነት ሊደፈር የማይችል ህጋዊ መብት ያስገኛል” ብሎ ለማሳመን በሚጥርበት በዚህ ወቅት፣ ይህ ውዝግብ ከቴክኒካዊ ጉዳይነት አልፎ መሠረታዊ ጥያቄ እየሆነ መጥቷል። አዳዲስ ባለአክሲዮኖች እንደ እውነተኛ ባለቤት የሚቆጠሩት አክሲዮኑን ከገዙበት ቅጽበት ጀምሮ ነው ወይስ መደበኛው የማረጋገጫ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ የሚለው ጥያቄ እየበረታ ነው።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት በበኩላቸው፣ በዚህ ዓመት የባለቤትነት ማረጋገጫው በይፋ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ለግል ባለአክሲዮኖች የሚደረገው የትርፍ ክፍፍል ድልድል በ2018/19 በጀት ዓመት እንደሚጀምር አስታውቀዋል።
PUBLISHED ON
May 26,2026 [ VOL
27 , NO
1361]
Photo Gallery | 187352 Views | May 06,2019
Photo Gallery | 177387 Views | Apr 26,2019
Photo Gallery | 173664 Views | Oct 06,2021
My Opinion | 140188 Views | Aug 14,2021
May 23 , 2026
An International Monetary Fund (IMF) team has spent weeks in Addis Abeba conducting t...
May 16 , 2026
The federal budget tells a troubling story about inflation, debt and reform. The prob...
May 9 , 2026
The Ethiopian state appears to have discovered a fiscal instrument that is politicall...
May 2 , 2026
By the time Ethiopia's National Dialogue Commission (ENDC) reached the end of its fir...