Photo Gallery | 190988 Views | May 06,2019
Jan 12 , 2026.
መንግሥታዊው የፖሊሲ ባንክ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (ኢልባ) በአመራር እርከኑ ላይ አምስት አዳዲስ ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ዛሬ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አግኝቷል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ብሩክ ታየ (ዶ/ር) በባንኩ ውስጥ ረጅም ዘመን ያገለገሉትን ጌታቸው ዋቄን በመተካት የኔነህ ግዛውን የኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል። በተመሳሳይ ጌታሰው ፈንታው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ዘርፍን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመድበዋል።
አቶ ጌታቸው በላይ የኮርፖሬት ደንበኞች አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት፤ አበባው ሲራጅ የፋይናንስና ዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት፤ እና ደሳለኝ ኃይሌ የኢንፎርሜሽን ሲስተምና ዲጂታል ባንክ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ብሩክ፣ የቀድሞውን የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተክተው የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑ ወዲህ በባንኩ የአመራር መዋቅር ላይ ፈጣን ለውጦች እየታዩ ነው። ሰሞኑን እመቤት መለሰን (ዶ/ር) በመተካት የባንኩ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን መሥራች አመራርነት በብሩክ ሥር ሲሠሩ የቆዩ መሆኑ ይታወሳል።
ፎርቹን የተመለከተው የቦርድ ሰብሳቢው የሹመት ደብዳቤና መግለጫ እንደሚያሳየው፣ አዲሶቹ ተሿሚዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሙሉ ቁርጠኝነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
PUBLISHED ON
Jan 12,2026 [ VOL
26 , NO
1342]
Photo Gallery | 190988 Views | May 06,2019
Photo Gallery | 180770 Views | Apr 26,2019
Photo Gallery | 177442 Views | Oct 06,2021
My Opinion | 143083 Views | Aug 14,2021
Jul 4 , 2026
In the goldfields of the Benishangul-Gumuz Regional State, Ethiopia's balance-of-paym...
Jun 27 , 2026
The federal legislative house rushed through one of the country's most contentious ho...
When Parliament takes up the appropriation bill, federal legislators will receive a d...
Jun 13 , 2026
The recent policy decision to fully open freight forwarding to foreign capital may be...