News Alert - Amharic | Jan 28,2026
ዓለም አቀፉ ፕሪሚየም ስማርት ስልክ ብራንድ TECNO ዛሬ ከሆሊሁዱ ኮከብ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስ ጋር ያለውን የንግድ ምልክት አምባሳደርነት ትብብር ቴክኖ አስታወቀ:: የሁለትዮሽ ትብብሩ ዝነኛው የቴክኖን “Stop At Nothing” የሚለውን ፍል ስፍና ለሰዎች በማንፀባረቅ እና ሰዎች በህይዎት የሚፈልጉዋችውን ነገሮች ለማሳካት ከሚያረጉዋቸው ሩጫዎች እንዳይቆጠቡ እና ሁልግዜም በልባቸው የወጣትነት መንፈስ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ እንዲያበረታታቸው የሚያደርግ ነው::
በማርቭል ዩኒቨርስ ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ ካፒቴን አሜሪካ በመሆን ሲተውን የሚታወቀው ክሪስ ኢቫንስ ከTECNO ጋር ሊያመሳስሉት የሚችሉብዙ ባህሪያት ያሉት ሲሆን በተለይም እያንዳንዱን ችግር በመወጣት የመጨረሻ ስኬትን ለማግኘት ያለው ታታሪነት ከቴክኖ ጋር አንድ ያደርጋቸዋል::
ክሪስ ኢቫንስ ከቴክኖ ጋር ስላለው ትብብር ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፥ "የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ሁልጊዜ ለማሙዋላት ከሚጥር እና ታዳጊ አገሮች ላይ ባሉ ገበያዎች ውስጥ ለተጠቃሚዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስፋፋ ካለው የቴክኖ የስማርትፎን ድርጅ ት ጋር የሚኖረኝን ትብብር በጉጉት እጠባበቃለሁ።በተጨማሪም በሆሊውድ ሰዎች ጥረታቸውን አንዳያቆሙ እና እክሎችን ሰብረው መሻገር እንዳለባቸው እና ልቀው ለመገኘት ጥረታቸውን አንዳያቆሙ እናነሳሳቸዋለን ። እንዲሁም ቴክኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለማቋረጥ በየጊዜው በመሻሻል ላይ ባለው የምርት ንድፍና ጥራት ላይ ይህንን መንፈስ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል። እንዲሁም በእነዚያ ታዳጊ አገሮች ላይ ሰዎች ተጨማሪ አማራጮችን እንዲመረምሩ እና ተመጣጣኝ አማራጮችን እንዲያዩ ማበረታታት ከማያቆም ታላቅ የንግድ ምልክት አጋር መስራት በእርግጥም ለስራ የሚያነሳሳ ነው።
የቴክኖ ሞባይል ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ስቲቨን ሃ እንዲህ ብለዋል፣ "TECNO ለብዙኃኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂ አማራጮችን ለማቅረብ ቃል የገባ ሲሆን ይህም ሸማቾች አሁን ካጋጠሟቸው የአቅም ገደቦች አልፈው የሚፈልጉትን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል:: በክሪስ ኢቫንስ ስራ ውስጥ የተወከለው የላቀ ችሎታ ያለማቋረጥ የመታተር መንፈስ ከቴክኖ የንግድ መርህ 'young at heart' ጋር ይዛመዳል:: እንዲሁም የተሻሉ አማራጮችን ለመፍተጠር በታዳጊ አገሮች ቴክኖ ከሚያደርገው መታተር ጋርም ይመሳሰላል:: በክሪስ ኢቫንስ የተንጸባረቀው ከሆሊውድ የመነጨው ዓለም አቀፋዊነት ስብዕናው እና የሚያምር የፋሽን ተከታይነትባሕርይ፣ የቴክኖ ምርት ንድፍና ባሕርያትን ያንጸባርቃል፤ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያምር፣ ጠንካራ፣ ዘላቂና የማያቋርጥ አቅኚነት ያለው እና የሰውን መንፈስ የሚስብ ነው። የሁለትዮሽ ስምምነቱ አሁን ባለን ደንበኞች መሠረት ውስጥ ለማደግ እና የንግድ ምልክታችንን አለማቀፍ ለማድረግ የሚያስችለንን አጋጣሚ እንደሚያመጣልን ጠንካራ እምነት አለኝ ብለዋል::
ከክሪስ ኢቫንስ ጋር ያለው ትብብር ከማንቸስተር ሲቲ የእግር ኳስ ክለብ ጋር ከነበረው ትብብር ቀጥሎ ለቴክኖ ሌላው አዲስ ምዕራፍ ከፋች ሲሆን በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አዳዲስ፣ የቴክኖሎጂና የዲዛይን እድገቶች አማካኝነት ወጣት ሸማቾች የማገልገል ችሎታ በማሳየት በዲዛይን ረገድ ምርጥ የሆኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር የታቀደው የቴክኖ ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት የማሳደግ ስትራቴጂ ክፍል ነው።
ክሪስ ኢቫንስ ግንቦት ላይ በሚደረገው የ CAMON 17 ምርት ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ላይ በበይነ መረብ በመገኘት ፕሮግራሙን ይመራል:: ስለዚህ ከታዳሚው ጋር በቀጥታ በበይነ መረብ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል::
PUBLISHED ON
May 18,2021 [ VOL
22 , NO
1099]
Dec 22 , 2024 . By TIZITA SHEWAFERAW
Charged with transforming colossal state-owned enterprises into modern and competitiv...
Aug 18 , 2024 . By AKSAH ITALO
Although predictable Yonas Zerihun's job in the ride-hailing service is not immune to...
Jul 28 , 2024 . By TIZITA SHEWAFERAW
Unhabitual, perhaps too many, Samuel Gebreyohannes, 38, used to occasionally enjoy a couple of beers at breakfast. However, he recently swit...
Jul 13 , 2024 . By AKSAH ITALO
Investors who rely on tractors, trucks, and field vehicles for commuting, transporting commodities, and f...
Jul 25 , 2026
Ideally, citizens who have paid income tax all year should not have to reach for thei...
Jul 18 , 2026
Pressed in Parliament on jobs and household incomes, Prime Minister Abiy Ahmed (PhD)...
Jul 11 , 2026
At a market stall, reform arrives without a communique. It comes as a higher transpor...
Jul 4 , 2026
In the goldfields of the Benishangul-Gumuz Regional State, Ethiopia's balance-of-paym...