መጋቢት 12/ 2014 አዲስ አበባ፣

ኢትዮጵያ፡ በአውሮፓ ህብረት እገዛ በኢትዮጵያ የንግድ ስራ አመቺነትን ለ ማ ሳ ለ ጥ እ የ ተ ተ ገ በ ረ ባ ለ ው ፕሮጀክት ስር የተከናወነ ጥናትን የተመለከተ ወርክሾፕ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓም ተካሄደ፡፡ ፡፡ ወርክሾፑ በኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር መስርያ ቤት ውስጥ ከፕሮጀክቱ በተገኘ ድጋፍ በኔትዎርከ ፤ ዳታ

ሴንተር እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ደህንነት መሰረተ ልማት ላይ የተደረገ ፍተሻና የተሻሻለ የኔትዎርክ ዲዛይንን ባካተተ ዶክመንት ላይ ሲሆን የገቢዎች ሚኒስቴር ተወካዮች እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ተወካዮች የተገኙበት ነበር፡፡




የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትዎርክ ማሻሻያ ስራው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የንግድ ስራ አመቺነትን ለማሳለጥ ያወጣውን የዲጂታላይዜሽን ሪፎርም ለመተግበር በገቢዎች ሚኒስትር ታቅዶ፣ በዚህ ፕሮጀክት ድጋፍ የተሰራ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ዓላማ በኢትዮጵያ ያለውን የንግድ ሁኔታ ማሻሻል፣ የግሉን ዘርፍ

ልማት ማበረታታት እንዲሁም የንግድ ስራ አመቺነትን በማሳለጥ የስራ እና የገቢ እድሎችን መፍጠር ነው፡፡




ፕሮጀክቱ ከየካቲት 2013 ጀምሮ  እስከ 2016 ድረስ ለሶስት አመታት ያህል የሚቆይ ሲሆን፣ በዚህ ፕሮጀክት ማዕቀፍ ውስጥ ድጋፍ የሚያገኙ ተቋሞች የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንዲሁም በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ቢዝነስ


ፎረም ናቸው፡፡

ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በተያያዘ ፕሮጀክቱ የቴክኒካል እና በተለያዩ ዘርፎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል፡ ፡ ይህም ድጋፍ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ምክረ ሀሳቦችን፣ ሞያዊ ድጋፍን እና ስልጠናዎችን አካቶ ይዟል፡፡በተጨማሪ በገቢዎች ሚኒስቴር ያለውን የግብር አሰባሰብ ስርዓት ቴክኒካል አቅም የማጎልበት እንዲሁም የመስርያ ቤቱን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኔትዎርክ የማሻሻል እገዛ ያደርጋል፡፡

በወርክሾፑ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ተወካይ በመክፈቻ ንግግራቸው በኢትዮጵያ መንግስት የግል ሴክተሩ በኢኮኖሚው የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ በተለይም የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢውን ምቹ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን እየተሰራ ያለውን የሪፎርም ስራ በማድነቅ የአውሮፓ ህብረት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡


የ ገ ቢ ዎ ች ሚ ኒ ስ ቴ ር ተ ወ ካ ይ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ የተከናወነው የኔትዎርክ ማሻሻል ስራ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት እየመራው ካለው የንግድ ስራ አመቺነትን የማሳለጥ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ እየተሰራ ላለው የዲጂታላይዜሽን ለ ው ጥ ክ ፍ ተ ኛ አ ስ ተ ዋ ፅ ዖ እንደሚያበረክት ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ምቹ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ እንዲሁም የዓለም ባንክ የ’Doing Business’ ደረጃዋን ማሻሻል እንዲቻል መንግስት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሃገራት ደረጃዋን እ.ኤ.አ በ2019 ከነበረችበት 159 ከፍ በማድረግ ከቀዳሚዎቹ መቶ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ለማስቻል ታህሳስ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት ብሔራዊ ኮሚቴ ተመስርቶ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው።



PUBLISHED ON Mar 28,2022 [ VOL 22 , NO 1144]


How useful was this post?

Click on a star to rate it!

Average rating 0 / 5. Vote count: 0

No votes so far! Be the first to rate this post.


Editors' Pick



Editorial




Back
WhatsApp
Telegram
Email