.

(ኪም ጆንግ ኡን) የቀጠለ...

(ኪም ጆንግ ኡን) የቀጠለ...


ጓዶች


የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ሁሉንም የህዝባችንን ድሎች ያቀናጃል እና ይመራል፡፡


የፓርቲያችን የማያልቅ ድል እና አይበገሬነት ታላቁን ፕሬዚደንት እና ጄኔራል እንደ እራሱ ዘላለማዊ መሪዎች አድርጎ በመያዙ እና ከሁሉም የኮሪያ ህዝብ ፍጹም ድጋፍ በመጎናጸፉ ላይ የሚመነጭ ነው፡፡


ፓርቲያችን ኮሪያን ወደ ብሩህ ጉዞ የሚመራ ከሆነ፣ እንደ ታላቁ ኪምኢልሱንግኢዝም-ኪምጆንግኢሊዝም ፓርቲ በመሆን፣ በሁለቱም ማለትም በስም እና እውነተኛነት አብዮታዊ ባህሪያቱን ያለምንም ድርድር መከላከል እና በእያንዳንዱ መንገድ ያለውን ብልህነት ከፍ አድርጎ ማሳየት አለበት፡፡


ታላቁ ኪምኢልሱንግኢዝም - ኪምጆንግኢሊዝም፣ በመሰረቱ የህዝብ ቅድሚያ መርህ እና የፓርቲያችን አኗኗር ህዝባችንን ማገልገል ነው፣


በታላቁ ፕሬዚዳንት እና ጄኔራል እውነተኛ የማስቻያ እሳቤዎች መሰረት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝብን ቅድሚያ የመስጠት እና የመውደድ ፖለቲካዊ አስተዳደርን ተግባራዊ ያደረጉ እና በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ለህዝቡ ጥሩ ነገር ለማድረግ እራሳቸውን አሳልፈው ለሰጡት ፓርቲያችን ለወደ ፊቱ ጭምር የህዝቡን የመጀመሪያ መርህ ቅዱስ ታሪክ ላይ ክብር ለመጨመር ይተጋል፡፡


አጠቃላይ ፓርቲው ግንባታ እና ተግባራቱን የሚያከናውነው በታላቁ ፕሬዝደንት እና ጄኔራል መመሪያ ብቻ ሲሆን ቅድሚያ ለህዝቡ የሚለውን መርህ በጥልቀት በአጠቃላይ ስራዎቹ ላይ ለማስፈጸም፣ በተቻለ መጠን በማንኛውም መንገድ የመዋጋት ብቃቱን በማዳበር እራሱን ትቶ ለህዝቡ ጥቅም እንዲያውል ለማድረግ ነው፡፡


የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ እውነተኛ ገጽታ በአመራሩ ስር በሚሸጋገረው የሀገሪቷ ገጽታ የሚገለጽ እና ሁል-ጊዜ በደስታ ፈገግታ በሚያሳዩት ህዝቦች ፊት ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡


ህዝቡ የሀገሪቷን አመሰራረት ያቋቋሙ በመሆናቸው እጅግ በጣም የከበሩ ናቸው፣ እና ከጥቅማቸው ውጭ ቅዱስ የሆነ ነገር የለም፡፡


ፓርቲያችን የህዝቡን ትሁት የሆነ ታማኝነት የአብዮቱ ታላቅ ሐብት አድርጎ ዋጋ ይሰጣል፡፡ እና ሁሉንም ሸክሞች በመሸከም እንዲሁም ለጀግና፣ በሐብት የተሞላ እና መልከመልካም ህዝባችን ፍላጎት እሾሀማ የሆነውን መንገድ በማጽዳት ለወደ ፊት የተቀመጠውን ግሩም ድንቅ ነገር አስቀድሞ እንዲመጣ እናደርጋለን፡፡


ለወደፊቱ ጭምር የማያልቅ ወሳኝነት እና የማይደክም ከፍተኛ ጉጉት የሞላውን ከባድ የሆነ ነገር ግን ቅዱስ የሆነ የእናት ፓርቲ ተልዕኮ ለማሟላት ጥረት በማድረግ፣ ለህዝቡ ካለው ጥልቅ ስሜት በመነሳት ሁልጊዜ የሚሰራ እና እራሱን ሙሉ በሙሉ ለጥቅማቸው አሳልፎ የሰጠ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ምንም አይነት ወጀብ ቢኖር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የህዝቡን የወደ ፊት እጣ ፈንታ በሚመለከት ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ መሰረታዊ ተግባሩ ነው፡፡


የኮሪያ አብዮት በማንኛውም ሚስጥራዊ ታላቅ ሐይል በሚፈጠር ከፍተት ወይም ጉድጓድ ወደ ፊት የሚራመድ ሳይሆን፣ ነገር ግን ጅግናውን የኪምኢልሱንግ፣ የኪምጆንግኢል የሰራተኛ መደብ ጨምሮ፣ ፓርቲያቸውን በአንድ አእምሮ በሚከተሉ እና በሚጠብቁ ህዝባችን ታላቅ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ፓርቲው ህዝቡን እንደ መንግስተሰማያት የሚያከብር እና የሚያምንበት እንዲሁም እንደ መካሪ እና ተቆጪ አድርጎ የሚወስድ፣ እና እናታቸውን እንደሚወዱት ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ገደብ የሚያምኑ እና የሚከተሉት ህዝቦች ናቸው፡፡ ይህ አንድ የሆነ የልብ ውስጥ መዋሐድ በአጭሩ የኮሪያ ትክክለኛ መገለጫ እና የሶንጉን አብዮት ታላቅ መሰረት ነው፡፡


ባለስልጣኖቻችን ልባቸውን መሙላት ያለባቸው ፓርቲው ህዝቡን ለማክበር ባለው ሐሳብ እና ለህዝቡ ባለው ስሜት ሆኖ፣ በረዶዋማ ሆነ ጭቃማ ማብቂያ ቢኖርም ትህትና እና ግልጽ የሆነ መንገድ የሚያስቀምጥ፣ ምኞታቸውን ሁሉ እንዲያስቡት የሚያደርገ ነው፡፡ በዚህ መንገድ በሀገሪቱ በአጠቃላይ ባለው አንድ የሆነ ልባዊ መዋሐድ እና ሶሻሊዝምን በማስተገባት የሰራተኞችን ፓርቲ አንድናቆት ለዘላለም ይኑር የሚል ድምፅ እንዲኖር የምናረጋግጥ ይሆናል፡፡


ፓርቲያችን ሁሉም አባላት የአገልግሎት ሰራተኞች፣ የህዝብ ጦር ወታደሮች እና ሰራተኛው ህዝብ፣ የስራ ቦታቸውን፣ ወታደራዊ ቦታ እና አካባቢ በሚመለከት በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ግቢው እንዳሉ ሆነው እራሳቸውን እንደሚቆጥሩ ያምናል፡፡ እና ሁል ጊዜ የውስጥ ሐሳባቸውን ከዚህ ጋር በማካፈል፣ ምንም እንኳን የሌለውን ታማኝነታቸውን እና የአርበኝነት ገድል ሐሳቦቹን ተግባራዊ በሚያደርግበት ጥረቶች ውስጥ እና ፖሊሲዎቹን ለማስጠበቅ እንደሚያውሉት ያምናል፡፡