.

(ኪም ጆንግ ኡን) የቀጠለ...

(ኪም ጆንግ ኡን) የቀጠለ...


ጓዶች


ለህዝቡ የሚታገለው የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ሃይል የሚመነጨው ጠንካራ የሆነ አብዮታዊ የታጠቀ የጦር ሃይል ያለው በመሆኑ ነው፡፡


ህዝባችን ጦር ያላነገበ ወይም ያልታጠቀ አገር መጥፋቱ የማይቀር መሆኑን በንቃት በመገንዘብ፣ የህዝቡ ክብር እና ደስታ በአብዮታዊ ጦሩ የሚረጋገጥ መሆኑን በእውነት ለማወቅ ችሏል፡፡


ፓርቲያችን በመጀመሪያ ደረጃ የማይበገር ወታደራዊ ጥንካሬ ያለው ሃይል ለመገንባት ትኩረት የሰጠ ሲሆን፣ በዚህም የህዝቡን ደህንነት ለመከላከል እና ኑሯቸውን እንዲሁም ንብረታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችለው ስራ ዘርግቷል፡፡


ለፓርቲያችን ዋነኛ ራስን የመቻል የመከላከያ ፖሊሲ እና ሶንጉን ፖለቲካ ምስጋና ይግባው እና የህዝቡ ጦር ማንኛውንም ወራሪ ሃይል በአንድ ምት መደምሰስ የሚችል ከፍተኛ አቅም ያለው አብዮታዊ ጦር እንዲሁም አድርጐ ገንብቶታል፣ እና መላው ህዝብ እንዲሁም መላው የአገሪቱ መከላከያ ዘዴ በዚህ ሲስተም ውስጥ በማያቋርጥ ሁኔታ ተጠናክረው ቀጥለዋል፣ የዚህም ውጤት በአሁኑ ጊዜ አገራችን ወደ ማይበገር ግንብ እንድትቀየር እና የአለም ታላቅ ወታደራዊ ሃይል እንድትሆን አስችሏል፡፡


አብዮታዊ ጦር ሐይላችን ሀገሪቷን የሚከላከል፣ የህዝቡን አብዮት የሚጠብቅ፣ እና በሀገሪቷ ብልጽግና ሂደት እንዲሁም የህዝቦቿ ደስተኝነት ትግል ውስጥ የመሪነት ድርሻውን የሚወጣ ሐይለኛ ግንባር ቀደም ሀይል እና አስደንጋጭ ብርጌድ ነው፡፡


የኢኮኖሚ ግንባታ ማስፋፊያ መስመርን ወደ ፊት በማስቀደም እና በተጓዳኝ የመከላከያ አቅማችንን በመገንባት፣ የሀገሪቷን መከላከያ ሀይል ከሶሻሊስት ግንባታ ጋር በመደበኛ ሁኔታ በማዋሐድ ፖርቲያችን በራሱ አጠቃላይ ብሔራዊ ጥንካሬን በፈጣን ሁኔታ በመጨመር እና በተመሳሳይ ማንኛውንም ነገሮች ያላገኘ ቢሆንም የህዝቡን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ዋጋ ያለው ተሞክሮ ያተረፈ ፓርቲ ነው፡፡


በወረራ እና በጦርነት ራሳቸውን ካወፈሩ ከዩናይትድ ስቴት ኢምፔሪያሊስቶች ግዙፍ እጆች ጋር ቀጥተኛ ፍልሚያ በማድረግ፣ የአገልግሎት ሰራተኞቻችን እና ህዝቡ በእነሱ ላይ አሳፋሪ የሆኑ ተከታታይ ሽንፈቶች አከናንቧቸዋል እናም የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች በጣሏቸው ቀማኛ ማዕቀቦች እና እገዳዎች ውስጥ በግድ እንዲሁም በኃይል ማለፍ ችለናል፡፡ በአንድነት ውስጥ ባለው የአልሸነፍ ባይነት መንፈስ እና ጥንካሬ በጠላት ላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት እና ፍርሃት ፈጥረናል፡፡


ዛሬ አብዮታዊ ጦር ሐይላችን የዩናይትድ ስቴት ኢምፔሪያሊስቶች የሚቀሰቅሱትን ማንኛውም አይነት ጦርነት ለመዋጋት አቅም ያለው መሆኑን ፓርቲያችን በኩራት ይገልጻል፣ እና በሀገሪቷ ድንበር ውስጥ ያለውን ሰማያዎሰማይ እና የህዝቡን ደህንነት ለመከላከል ሙሉ ዝግጅት አድርጓል፡፡


ጓዶች


የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ልዩ የሆነ የኩራት ስሜት ምንጭ የሚሆነው የአብዮቱን እና የሀገሪቷን የወደ ፊት ሁኔታ ለመሸከም ስልጠና በወሰዱት ትልቅ የወጣት ኃይል ላይ ነው፡፡


አብዮቱ በምስረታ ጊዜ የነበረውን የተራዘመ ሂደት አስቀድሞ በማሰብ ፓርቲያችን እንደ ስትራቴጂካዊ መስመር የወጣቱን ኃይል አስፈላጊነት ላይ በማተኮር የጁቼ አብዮት አላማ እና ፍላጎት ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስችሏቸውን የተዋጊነት ስልጠና ሰጥቷቸዋል፡፡


አጠቃላይ ፓርቲው ወጣቶችን ለማስተማር ቋሚ የሆነ እሳቤ በመያዝ፣ የወጣቱን ሊግ ከታላላቅ ፕሮጀክቶች ጋር ፈርጣማ የሆነ ስራ ላይ መድቧል፡፡ እንደ አንድ ወጣት ግምባር ቀደም ሐይል ወደ ፊት ያራመዳቸውን ፓርቲ ላይ ባላቸው እምነት እና ስሜት ወጣቶችን በብሔራዊ መከላከያ ዘመቻዎች ውስጥ በማንኛውም ቦታ እና በማንኛውም ጊዜ ለማገልገል ሙሉ በሙሉ ፈቃደኝነቱን የገለጸ እና እንዲሁም በአስቸጋሪ እና ፈታኝ በሆኑ ዘርፎች ጭምር የሰራ በመሆኑ፣ እና የወጣትነት ጥበብ እና ጀግንነታቸውን እስከመጨረሻው ያሳዩ ናቸው፡፡


አብዮታችን እስከ አሁን ድረስ በማይሟጠጥ ሀይል በሀይለኝነት በመሞላት ወደ ፊት የሚራመድ እና ባለበት የማይቆም ወሳኝነት ያለው እንዲሁም የምልክት ጊዜ ብቻ የሚጠብቅ ፓርቲውን በመከተል ሁል ጊዜ በቀጥታ ወደ ፊት የሚዘምት እንደ ብረት የጠነከረ የወጣት መቅኔ ያለው ነው፡፡


በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉት የኩራት እና የታላቅነት ምልክት የሆኑት የወጣቶች ሐውልቶች፣ የፔክቱሳን ጀግና ወጣት ሀይል ማመንጫ ጣብያን ጨምሮ፣ ወጣቶችን የአርበኝነት ላባቸውን በመገበር በቅርብ ጊዜ የመሰረቱት እና ለ70ኛው አመት የፓርቲ ምስረታ የተሰጠውን፣ የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ተጠባባቂ ሀይል እንዴት እንደሚዘጋጅ እና የኮሪያ አብዮት የዘር አወራረድ እንዴት ወደ ፊት መጓዝ እንደሚኖርበት በግራፍ ምስል የሚያሳይ ነው፡፡


ፓርቲያችን ለወጣቶች ያወጣው ምንም ነገር ባለመኖሩ ሀገራችን በወጣት እንቅስቃሴ ላይ በትኩስ የሆነ የአፍላ ጊዜ እያስተናገደች ነች እና ይህ እንደ አንድ እና ብቸኛ ታላቅ የወጣት ሀይል ሆኖ ሐይሉን በማሳየት ላይ የሚገኝ፣ እንዲሁም የወጣቱ ጉዳይ በትክክል ማከናወን እየገለጠ ያለ ነው፡፡


የአብዮታዊው ፓርቲ የሕይወት መስመር ጥንካሬው እና የወደፊት ደማቅ ጉዞ ከህዝቡ፣ የጦር ሀይል እና የወጣቱ ኃይል ጋር በሚያያይዘው አስፈላጊነት ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ይህም ማለት ተወዳዳሪ የሌለው የፓርቲያችን የ70 አመታት ታሪክ ድምር ውጤት ነው፡፡

የህዝቡን፣ የጦር ኃይሉን እና የወጣቱን ኃይል እንደ ቀዳሚ መሳሪያነት ያለውን ጠቃሚነት ማያያዣ የሚሆነውን ባለ ሶስት ነጥብ ስትራቴጂ አጠናክሮ በመቀጠል፣ ፓርቲያችን በሀይለኝነት ስሜት ወደ መጨረሻው ድል ለመድረስ እና የኮሪያን አብዮት ለማከናወን ወደ ፊት ይራመዳል፡፡