.

(ኪም ጆንግ ኡን) የቀጠለ...

(ኪም ጆንግ ኡን) የቀጠለ...


ጓዶች


የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ታሪክ የህዝቡን እጣ ፈንታ በመሸከም እና የኮሪያን አብዮት ወደ ድል በመምራት በታላላቆቹ መሪዎች መመሪያ ስር ያደረገው ኩራት የተሞላበት የጉዞ ታሪክ ነው፡፡


ፕሬዚዳንት ኪም ኢልሱንግ እና ጀኔራል ኪም ጆንግ ኢል እኛን ወደ የማይበገር አብዮታዊ ፓርቲ ፣ እውነተኛ ፖለቲካዊ አመራር ያለው ድርጅት እንዲሆን በማስቻል የገነቡን ሲሆን ይህም ህዝቡን የሚያገለግል እና ከሰፊው ህዝብ ጋር በአንድነት ወደፊት የሚራመድ በታሪክ የመጀመሪያው ፓርቲ ነው፡፡


በቀዩ ባንዲራው ላይ የቀረጻቸው መዶሻ፣ ማጭድ፣ መጻፊያ ብሩሽ መሠረት፣ ፓርቲያችን ከህዝቡ ተነጥሎ አያውቅም እንዲሁም ልክ በመንግስተ ሰማያት እንደሆኑ በማመን ሁልጊዜ አብዮቱን እያራመደ ይገኛል፡፡


በታሪክ ውስጥ ልክ እንደእኛ የተመዘገበ በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ ጀግንነት የተሞላበት፣ የከፋ ታሪካዊ ፍርደ ገምድልነት እና ባለአጋራ ወገኖች የታዩበት እና በእንደዚህ በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ ሁኔታ ውሰጥ ወሳኝ የሆነ ስኬት ያስመዘገበ አብዮት የለም፡፡


አዲሲቷ ኮሪያ በጣም ወጣት ነበረች፣ ነገር ግን የዩናይትድ ስቴት ኢምፔሪያሊስቶች፣ በአለም የበላይነት ላይ ለማሳየት በሚያደርጉት እብድ ምኞት፣ አፍራሽ የሆነ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ አስገድደውታል፣ አገሪቷን ከፍርስራሾቿ አንስተን መልሰን ስንገነባት ቀበቷችንን አጥብቀን ከፍተኛ ጥረት ያደረግን ሲሆን፣ እነርሱ ግን ሌላ ትኩስ የወረራ ስጋት አሳድረውብናል፡፡ ብሔራዊ ኢኮኖሚያችንን ለማሳደግ በምንጥረበት ጊዜ፣ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ማእቀብ በመጣል እና የተለያዩ የንግድ መስመሮችን በመዝጋት ያሉንን መዳረሻ መንገዶች ሁሉ ዘግተውታል፡፡


እነዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም፣ ፓርቲያችን በማንኛውም ባለአጋራ ሃይል ላይ ያለውን ብረት ለበስ ነርቮች ወደፊት መራመዱን የቀጠለ ሲሆን፣ በዚህ መሬት ላይ አዲስ የታሪክ ምእራፍ በመጻፍ ታላላቅ የሆኑ ድሎችን አስቆጥሯል፡፡


በታሪክ እሽክርክሪት ውስጥ፣ ፓርቲያችን የሚያምነው ታላቁን ህዝባችንን ብቻ ነበር፣ እናም ብቸኛ ደጋፊዎቻችን፣ አማካሪዎቻችን እና ረዳቶቻችን ህዝባችን ነበር፡፡


የአለም አብዮታዊ እንቅስቃሴ ታሪክ ረጅም ታሪክ ያለውም ሆነ በአገዛዝ ላይ የሚገኝ ቢሆን እንኳን፣ የአንድ ገዢው ፓርቲ የአመራር ስልጣን እንዲሁም የጦርነት ብቃት በራሱ ዝም ብሎ ሊነሳ አይችልም፣ አብዮቱንም በብቃት ብቻ መምራት አይችልም፡፡


ዛሬ ፓርቲያችን የተጐናፀፈው ከፍተኛ ስልጣን እና ያከናወናቸው ታላላቅ ስራዎች እና አብዮቱን በህዝቡ ላይ ባላቸው እምነት ስሜት የቀረጹ እና ይህንን ትርጓሜ ወደ ግንባታ እና ተግባር የቀየሩ ደማቅ የሆነው የአብዮታዊ ሀሳቦች አፍላቂ እና ግንባር ቀደም መሪዎች የነበሩት የታላቁ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ጀኔራል ያመጡት ፍሬ ነው፡፡


ፓርቲያችን የነጻነትን ምክንያታዊ ውጤት ሚስጢር የሚያርፈው፣ ነጻነት፣ ሶንጉን እና ሶሻሊዝም በታሪክ ውጣ ውረድ ውስጥ በማለፍ የአብዮቱን የእንቅስቃሴ አቅጣጫ አመራር ላይ ጠንካራ የሆነ መዳፍ በማሳረፍ ላይ መሠረቱን በህዝቡ አእምሮ ውስጥ በጥልቅ በመጣል እና በታላቅ የፍቅር ስሜት ብቻ በማገልገል ላይ ነው፡፡


የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ በሰፊው ህዝብ ውስጥ የአንድነት ስሜት መፍጠር የቻለ የማይበገር ፓርቲ ነው፡፡


አብዮቱን በመምራት ሂደት ውስጥ በነበረው በሁሉም ጊዜ ውስጥ፣ ፓርቲያችን በመጀመሪያ ህዝቡን በመጥራት፣ አስተያየታቸውን በማዳመጥ፣ ቀላል ቢሆንም ከትህትናቸው ውስጥ የማይቆረጥ ጀግንነት በማውጣት በማንኛውም አንድ ሁኔታን ለመለየት በሚሞክርበት ጊዜ መከተል የሚገባውን እና በማንኛውም የከፋ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ማድረግ የሚጠበቅበትን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡


ምንም የማይሳነው የሰፊው ህዝብ ፈጠራ የታከለበት ጥንካሬ ፓርቲያችን በጣም ጠንካራ የሆነውን የሶሻሊስት ጋሻ፣ ነጻነት፣ በብሔራዊ መከላከያ በኩል ራስን ለመደገፍ እና ራስን ለመቻል ባደረገው ግንባታ ወቅት የነበሩት ታላላቅ የድንቃድንቆች ምንጭ ነበር፡፡ በዚህ መሬት ላይ የ100 አመታት የኋላ ቀርነት እና ድህነት የተንሰራፋበት የነበረ ሲሆን፣ በኢምፔሪያሊስቶች አማካኝነት የተጣለብንን ጐጂ የሆነ ውጤት ያለው ማእቀብ እና እግድ በመቋቋም አዲስ እና ጠንካራ የሆነ የአገር ግንባታ ምእራፍ ከፍተናል፡፡


ለህዝቡ ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች ቅንነት እና የማቴሪያል እንዲሁም የባህላዊ ኑሮ ሙሉ ሃላፊነት በመውሰድ፣ እና ለእነርሱ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የፓርቲያችን ግንባር ቀደም አጀንዳ ነበር፣ እንዲሁም ለአፍታ ያህል እንኳን ሊዘነጋ የማይችል ተልእኮ ነበር፡፡


ፓርቲያችን፣ የአገራችን እጣ ፋንታ ወሳኝ በሆነው እጅግ በጣም የከፋ ሁኔታ ውስጥ እንኳን፣ ለህዝቡ ደስታ በማሰብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ እና ለህዝቡ ፍቅር የተሞላበት ፖለቲካ ለመግለጽ ህዝቡን ያማከለ ፖሊሲዎች ላይ ሁልጊዜ ሳያቋርጥ በመስራት፣ ህዝቡ ለወደፊት እጣ ፋንታው ሃላፊነቱን በተሸከመለት ፓርቲ የሚመራበትን እጅግ ውድ የሆኑ የአመራር ዘር እና ሶሻሊስት ሃብቶች አዘጋጅቷል፡፡


ፓርቲያችን ሰፊውን ህዝብ ሁልጊዜ የራሱ ኑሮ መሠረት አድርጐ የሚቆጥር በመሆኑ እና የማያልቅ ጥንካሬ ምንጭ መሆኑን በማሰብ፣ ለህዝቡ ጥቅም ግንባር ቀደም ፍጹም የሆነ ቅድሚያ ሰጥቷል፡፡ ህዝባችን ፓርቲውን የሚከተለው የወደፊት እጣ ፋንታውን እንዲደርስ የሚመራው እውነተኛ መብራት መሆኑን በማመን እና እንደ እናት ፓርቲ በመቁጠር ስለሆነ፣ በአንድ ልብ የተዋሀደ ስሜት ያለው ታላቅ የአትክልት ቦታ በዚህ መሬት ላይ በኩራት ብቅ ማለት ችሏል፡፡