.

SPONSORED CONTENT

ኪም ጆንግ ኡን

ከራስ በላይ በማለፍ፣ ለህዝቡ መልካም ነገር ለማድረግ እራስን አሳልፎ በመስጠት ጥረት ማድረግ
የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ የህልውና ዘይቤ እና የማይበገር
ሐይል ምንጭ ነው፡፡

በኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ 70ኛ አመት የምስረታ በዓል ስነ-ስርዓት ላይ በተደረገው
የፒዮንግያንግ ዜጎች ወታደራዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ ትዕይንት

መስከረም 29፣ 2008
(October 10, 2015)

.

SPONSORED CONTENT

ኪም ጆንግ ኡን

ከራስ በላይ በማለፍ፣ ለህዝቡ መልካም ነገር ለማድረግ
እራስን አሳልፎ በመስጠት ጥረት ማድረግ የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ
የህልውና ዘይቤ እና የማይበገር
ሐይል ምንጭ ነው፡፡

በኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ 70ኛ አመት
የምስረታ በዓል ስነ-ስርዓት ላይ በተደረገው
የፒዮንግያንግ ዜጎች ወታደራዊ ሰልፍ እና
ህዝባዊ ትዕይንት

መስከረም 29፣ 2008
(October 10, 2015)


ጀግኖች የጦር መኮንንኖች እና የኮሪያ ህዝብ ጦር ወታደሮች እንዲሁም የኮሪያ ህዝብ የአገር ውስጥ ደህንነት ሃይሎች፣


የተከበራችሁ የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ 70ኛ የምስረታ አመት አከባበር ስነስርአት ላይ በተደረገው ወታደራዊ ሰልፍ የተሳተፋችሁ መኮንኖች እና የቡድን አባላት፣


የሰራተኛ - ገበሬ ቀይ ጠባቂዎችና እና የወጣት ቀይ ጠባቂዎች አባላት


የተከበራችሁ የፒዮንግያንግ ከተማ ነዋሪዎች፣


የፓርቲ አባላት እና ሌሎች በአገሩ ዙሪያ ያላችሁ ሰራተኞች


በውጪ አገር ያላችሁ ወገኖች እና የውጪ አገር ወንድሞች፣


ጓዶች


ዛሬ በድል አድራጊነታችን ባገኘነው ታላቅ ክብር እና ደስታ፣ የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ባንዲራ በሰማይ ላይ ከፍ አድርገን እያውለበለብን የጥቅምት በአልን እያከበርን እንገኛለን፡፡


ለአገራችን እና ለህዝባችን፣ ይህም እውነተኛውን የአብዮቱን ግንባር ቀደም ተሰላፊ፣ አማጺ የሆነው የጠቅላላ ሰራተኛ አባላትን ሃላፊነት በመውሰድ እጣ ፈንታቸውን ለዚህ አላማ በማዋል እና የመሩትን የትውልድ ቀን በአል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ ጥቅምት 10 ትርጉም ያለው አብዮታዊ በአል ነው፡፡


በዛሬው እለት ፓርቲያችን የአገልግሎት ሰጪ ሰራተኛውን እና ህዝቡን በመምራት ባለፉት 70 አመታት ውስጥ የገነባውን እና ሙሉ በሙሉ ተሟጦ የማያልቅ ጥንካሬ የሚያሳይ ታላቅ የሆነ ወታደራዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ ትእይንት ይቀርባል፡፡ በተጨማሪም የሁሉንም የአገልግሎት ሰጪ ሰራተኞቻችን እና ህዝባችን፣ በጀግንነት እና ቁርጠኝነት የተሞላ፣ ብሩህ የሆነ የወደፊት ተስፋ ሰንቆ የሚጓዝ እና በኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ዙሪያ በአንድነት የተዋሃደ አብዮታዊ መንፈስ ያለው መሆኑን ለመላው አለም ያሳያል፡፡


በዚህ አጋጣሚ ባገኘሁት እድል በድል እና በክብር ያሸበረቀውን የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ ቅዱስ የሆነ ታሪክ ወደኋላ ተመልሰን በማስታወሳችን ኩራት ይሰማናል፡፡ በዚሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት እና የሁሉም ወታደሮች፣ ህዝቦች ያላቸውን ታማኝነት እና ድንበር የለሽ አምልኮ የሚያንፀባርቅ፣ ታላቁን ፓርቲያችንን ለመሰረቱት የታላቁ ጓድ ኪም ኢልሱንግ እና የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲ የቋሚ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን ጓድ ኪም ጆንግ ኢል የተከበረ እጅግ በጣም ከፍ ያለ እና የማያልቅ ክብር ለመስጠት እወዳለሁ፡፡


ከዚህ በተጨማሪ ለፀረ ጃፓን አብዮታዊ እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሰማእታት፣ የህዝብ ጦር ሰማእታቶች፣ ለፓርቲያችን ልማት እና እድገት ያላቸውን ውድ ነገሮች በማዋል ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ሌሎች ጀግኖች ሰማእታት እንዲሁም በታላቆቹ መሪዎች በመታመን ለሀገራችን ብልጽግና ድጋፍ ለሰጡት ሁሉ ያለኝን ከፍ ያለ ክብር መስጠት እወዳለሁ፡፡


ህዝባችን ለፓርቲው ባለው የማያወላውል ታማኝነት 70ኛውን አብዮታዊ ምስረታ በአል ለማጉላት በፓኬቱ የቀዩ አብዮታዊ መንፈስ ላይ ያጋጠሙትን ሁሉንም ተግዳሮቶች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች፣ በአንድነት በመወጣት ተስፋ ያለው ሁኔታ እንዲፈጠር ከማስቻሉም በላይ፣ ተወዳዳሪ የሌለው ከፍተኛ የሰራተኛ ጀብዱ አከናውኗል እና ለእናት ፓርቲው የሚሆኑ ስጦታዎችን አዘጋጅተዋል፡፡


በአሁኑ ጊዜ በድል አድራጊዎች አደባባይ ቆሜ፣ የስነስርአቱ አከባበር ጐዳና ላይ ሆኜ ህዝባችን ባለው ከውስጥ የመነጨ ታማኝነት ላይ አፌን ሞልቼ ለመናገር በመቻሌ፣ ከእነሱ በተናጠል ይህ በፍጹም ሊታሰብ የማይችል ዛሬ የቆምኩበት አደባባይ ላይ ሆኜ በመናገሬ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፣ እና በዚህ ሰአት ውድ የሆነውን ለህዝባችን ያለኝን ጥልቅ የሆነ ክብር ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡


ፓርቲያችን ምንም አይነት አውሎንፋስ እንኳን ቢያጋጥመው ያለምንም ማፈግፈግ አብዮቱን ባለፉት 70 አመታት ውስጥ በሚፈለገው ፍጥነት በማክነፍ ድላችንን እና ክብራችን እንድናገኝ አስችሎናል፡፡ በዚህ ታላቅ ህዝብ ምክንያት የራሳቸውን እጣ ፋንታ ለዚህ አላማ በመሰዋት እና ለውጤቱ በእምነት በመቆም እና ድጋፍ በማድረግ እስከአሁን ድረስ እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡


የፓርቲያችን ታሪክ በታላቁ ህዝባችን የተደረገ የጉዞ መስመር ነው፡፡ የፓርቲያችን ሃይል የማመነጨው ከእነዚህ ህዝቦች ሃይል ነው፡፡ ታላቅነቱን የእነዚህ ህዝቦች ታላቅነት ሲሆን ድሉም የተገኘው በእነሱ ድል አማካኝነት ነው፡፡


በፓርቲው 70ኛ አመት የምስረታ በአል አከባበር ስነስርአት ላይ፣ እኔ የኮሪያ ሰራተኞች ፓርቲን በመወከል ፓርቲያችንን ምንጊዜም የማያልቅ ጥንካሬ እና ጀግንነት የሞሉትን እና በእያንዳንዱ የአብዬቱ አስከፊ ጊዜ ወቅት በታማኝነት ለቆየው ለተወደደው ህዝባችን ዝቅ ብዬ ሞቅ ያለ ሰላምታ ለመስጠት እወዳለሁ፣ የታሪክን የከፋ ሂደት በመቋቋም ደስታ እና ሃዘንን በመጋራት የማይበገር ተስፋ ያለው ሃይል መሆናቸውን በማሳየታቸው ላመሰግን እወዳለሁ፡፡


ለፓርቲው ጠንካራ አባላት፣ ጀግኖች መኮንኖች እና የህዝብ ጦር ወታደሮች እንዲሁም የሚመሰገን ወጣት ግንባር ቀደም ሃይል፣ ፓርቲው ላቀረበው ቅሬታ ለሰጡት ከልብ የመነጨ ያለኝን ልባዊ ምስጋና በማቅረብ፣ በአርበኝነት መንፈስ ለሰሩት እና ከአንድ የጀግንነት ጀብዱ በመቀጠል ሌላ ጀብዱ እየፈጠሩ 10 አመታትን ወደ አንድ በማሳጠር በሁሉም ግንባሮች የዳበረ ሶሺያሊስት አገር ለገነቡት፣ እና ታላቁን የድል አድራጊዎች ፌስቲቫል ጐዳና በኩራት እንድንገባ ማስቻሉን ያለኝን ልባዊ ምስጋና እገልጻለሁ፡፡


በተመሳሳይ በውጪ አገር የሚገኙ ወገኖቻችን እና የውጪ አገር ጓደኞቻችን በዚህ ተስፋ ሰጪ ቀን ላይ ተገኝተው ለህዝባችን እንኳን አደረሰህ ለማለት የመጡትን ሁሉ ሞቅ ያለ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡