ዓለም አቀፉ ፕሪሚየም ስማርት ስልክ ብራንድ TECNO ዛሬ ከሆሊሁዱ ኮከብ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስ ጋር ያለውን የንግድ ምልክት አምባሳደርነት ትብብር ቴክኖ አስታወቀ:: የሁለትዮሽ ትብብሩ ዝነኛው የቴክኖን “Stop At Nothing” የሚለውን ፍል ስፍና ለሰዎች በማንፀባረቅ እና ሰዎች በህይዎት የሚፈልጉዋችውን ነገሮች ለማሳካት ከሚያረጉዋቸው ሩጫዎች እንዳይቆጠቡ እና ሁልግዜም በልባቸው የወጣትነት መንፈስ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ እንዲያበረታታቸው የሚያደርግ ነው::

በማርቭል ዩኒቨርስ ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ ካፒቴን አሜሪካ በመሆን ሲተውን የሚታወቀው ክሪስ ኢቫንስ ከTECNO ጋር ሊያመሳስሉት የሚችሉብዙ ባህሪያት ያሉት ሲሆን በተለይም እያንዳንዱን ችግር በመወጣት የመጨረሻ ስኬትን ለማግኘት ያለው ታታሪነት ከቴክኖ ጋር አንድ ያደርጋቸዋል::


ክሪስ ኢቫንስ ከቴክኖ ጋር ስላለው ትብብር ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፥ "የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ሁልጊዜ ለማሙዋላት ከሚጥር እና ታዳጊ አገሮች ላይ ባሉ ገበያዎች ውስጥ ለተጠቃሚዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስፋፋ ካለው የቴክኖ የስማርትፎን ድርጅ ት ጋር የሚኖረኝን ትብብር በጉጉት እጠባበቃለሁ።በተጨማሪም በሆሊውድ ሰዎች ጥረታቸውን አንዳያቆሙ እና እክሎችን ሰብረው መሻገር እንዳለባቸው እና ልቀው ለመገኘት ጥረታቸውን አንዳያቆሙ እናነሳሳቸዋለን ። እንዲሁም ቴክኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለማቋረጥ በየጊዜው በመሻሻል ላይ ባለው የምርት ንድፍና ጥራት ላይ ይህንን መንፈስ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል። እንዲሁም በእነዚያ ታዳጊ አገሮች ላይ ሰዎች ተጨማሪ አማራጮችን እንዲመረምሩ እና ተመጣጣኝ አማራጮችን  እንዲያዩ ማበረታታት ከማያቆም ታላቅ የንግድ ምልክት አጋር መስራት በእርግጥም ለስራ የሚያነሳሳ ነው።

የቴክኖ ሞባይል ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ስቲቨን ሃ እንዲህ ብለዋል፣ "TECNO ለብዙኃኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂ አማራጮችን ለማቅረብ ቃል የገባ ሲሆን ይህም ሸማቾች አሁን ካጋጠሟቸው የአቅም ገደቦች አልፈው የሚፈልጉትን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል:: በክሪስ ኢቫንስ ስራ ውስጥ የተወከለው የላቀ ችሎታ ያለማቋረጥ የመታተር መንፈስ ከቴክኖ የንግድ መርህ 'young at heart' ጋር ይዛመዳል:: እንዲሁም የተሻሉ አማራጮችን ለመፍተጠር በታዳጊ አገሮች ቴክኖ ከሚያደርገው መታተር ጋርም ይመሳሰላል:: በክሪስ ኢቫንስ የተንጸባረቀው ከሆሊውድ የመነጨው ዓለም አቀፋዊነት ስብዕናው እና የሚያምር የፋሽን ተከታይነትባሕርይ፣ የቴክኖ ምርት ንድፍና ባሕርያትን ያንጸባርቃል፤ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያምር፣ ጠንካራ፣ ዘላቂና የማያቋርጥ አቅኚነት ያለው እና የሰውን መንፈስ የሚስብ ነው። የሁለትዮሽ ስምምነቱ አሁን ባለን ደንበኞች መሠረት ውስጥ ለማደግ እና የንግድ ምልክታችንን አለማቀፍ ለማድረግ የሚያስችለንን አጋጣሚ እንደሚያመጣልን ጠንካራ እምነት አለኝ ብለዋል::



ከክሪስ ኢቫንስ ጋር ያለው ትብብር ከማንቸስተር ሲቲ የእግር ኳስ ክለብ ጋር ከነበረው ትብብር ቀጥሎ ለቴክኖ ሌላው አዲስ ምዕራፍ ከፋች ሲሆን በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አዳዲስ፣ የቴክኖሎጂና የዲዛይን እድገቶች አማካኝነት ወጣት  ሸማቾች የማገልገል ችሎታ በማሳየት በዲዛይን ረገድ ምርጥ የሆኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር የታቀደው የቴክኖ ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት የማሳደግ ስትራቴጂ ክፍል ነው።

ክሪስ ኢቫንስ ግንቦት ላይ በሚደረገው የ CAMON 17 ምርት ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ላይ በበይነ መረብ በመገኘት ፕሮግራሙን ይመራል:: ስለዚህ ከታዳሚው ጋር በቀጥታ በበይነ መረብ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል::




PUBLISHED ON May 18,2021 [ VOL 22 , NO 1099]


How useful was this post?

Click on a star to rate it!

Average rating 0 / 5. Vote count: 0

No votes so far! Be the first to rate this post.

Put your comments here

N.B: A submit button will appear once you fill out all the required fields.


Editors' Pick



Editorial




Back
WhatsApp
Telegram
Email